የማስተዋል ግብዣ 1
አንድ ሰው ወደ ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሃንበል ዘንድ በመምጣት እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡-
ጠያቂው፡- አንቱ ኢማሙ አህመድ ሆይ! ከሰዎች ሰላም የምሆንበት መንገድ እንዴት ነውን?
ኢማሙ አህመድ እንዲህ አሉት ፡ ያንተን ትሰጣቸውና - የእነሱን ያልተቀበልክ እንደሆን ፣
እነሱ አንተን እያስቸገሩህ - አንተ ደግሞ የማታስቸግራቸው ከሆነ ፣
አንተ የእነሱን ጉዳዮች እየፈፀምክላቸው - እነሱ ደግሞ ያንተን ጉዳይ እንዲፈፅሙልህ የምታስገድዳቸው ካልሆንክ ... ከእነሱ ሰላም መሆን ትችላለህ ይሉታል ፡
ከዚያ ሰውዬው እንዲህ አላቸው ፡ አንቱ ኢማሙ አህመድ ሆይ ! ይሄን ማድረግ እጅጉን ይከብዳል'ኮ!!
ከዚያም እርሳቸው እንዲህ አሉት ፡ እስኪ ዝም በል ! ይሄንንም ሁሉ አድርገህ ከእነሱ ሰላም በሆንክ!!
ምንጭ፡- ሲየር አዕላሙ ኑበላዕ ( 11-12 )
የማስተዋል ግብዣ 2
አንዲት ሴት ወደ ታዋቂው ዳኛ ሸዕቢይ ዘንድ በመሄድ ባሏን ከሰሰች።
ክሷን ስታቀርብም በለቅሶ ታጅባ ነበር። ዳኛው በለቅሶዋ ስሜቱ በመነካቱ ተከሳሽ ወደሆነው ባሏ ዘወር ብሎ " ይህች ሴት በጣም የተበደለች ይመስለኛል " አለው ።
ባሏም " የነቢዩላህ ዩሱፍ ወንድሞችም በምሽት ወደ አባታቸው ዘንድ ሲመለሱ እያለቀሱ ነበር ። ነገር ግን ተበዳዮች ሳይሆኑ በዳይ ነበሩ ።
የማስተዋል ግብዣ 3
የአእምሮን እድገት ከሚጨምሩ ነገሮች ውስጥ አንድና ዋነኛው አስተዋይ መሆን ነው። ያየውን ሁሉ የሚናገር ህጻን ልጅ፣ የሰማውን ሁሉ የሚያወራ ውሸታም፣ የተመኘውን ሁሉ የሚጠብቅ ሞኝ ነው። ያልታረሰ መሬት ላይ የተዘራ ዘር በአረም ይዋጣል። ሳያረጋግጥ የሚያወራ ጥርጣሬ ህሊናውን ይጎረብጠዋል። አንድ አይኑን አጥቶ ሲያለቅስ ያየኸው ሰው ሁለት አይን አጥፍቶ ሊሄን ይችላል። እጁ ተቆርጦ ያየኸው ሰው ገሎ ሊሆን ይችላል።
ለማረጋገጥ መረጃ፣ ላለመታለል መጠንቀቅ፣ ላለመጠርጠር አጢኖ ማስተዋል ያስፈልጋል።
መራር እውነታዎች
1
ዶክተር ገርቢያ አልገርቢ ትባላለች። በሙያዋ ዶክተር ናት። እንዲህ ስትል አስተዋዮችን ታናግራለች፦
"እጅግ አደገኛ እና ውስብስብ የሆኑ ቀዶ ጥገናዎች በሰው ልጅ ወሳኝ ክፍሎች ላይ ይካሄዳሉ። በአእምሮውና በልቡ ላይ። ህይወቱ ባጠቃላይ በነዚህ ክፍሎቹ ላይ የተንጠለጠለ ነው።
-ይህን ቀዶ ጥገና የሚያካሂደው ሰፋፊ አልባሳት የለበሱ ፣ እራሳቸውን የሸፈኑ ፣ የፊት መሸፈኛ የለበሱ ፣ የእጅ ጓንቶችም ያጠለቁ ሰዎች ያሉበት የህክምና ቡድን ነው።
ይህ አለባበሳቸው ግን ለዚህ ውስብስብና አደገኛ ስራ እንቅፋት አልሆነባቸውም።
-ከዚያ ግን "ሒጃብና ኒቃብ ስራን ፣እድገትንና ስልጣኔን ከሚያደናቅፉ እንቅፋቶች ውስጥ ናቸው' የሚል ሰው ታያለህ!!"
2
እናት፡ ብሩን የት እንደምደብቀው አላውቅም ልጄ ሁሉም ቦታ ብደብቀው ያገኘዋል ።
ጎረቤት፡ መፅሀፍ ውስጥ ደብቂው እዛ ከሆነ መቼም አያገኘውም።
ከሰለፎች
ሐሰን አልበስሪ አንድ ሰው ክፉኛ እንዳማቸው አወቁና ጣፋጭ ቴምርና አነስተኛ መልእክት ላኩለት፤ መልእክቱም ወዳጄ ሆይ እንደምን ሰንብተሀል እንዳማኸኝ ባወቅኩ ጊዜ ይህን ጣፋጭ ቴምር ላኩልህ አምተኸኛል ብዬ አምቼህ ያገኘሁትን ምንዳ በዋዛ የማስነጥቅ ሞኛሞኝ አይደለሁም የሚል ነበር።
"ንጉሶችና የንጉሶች ልጆች እኛ ያለንበትን ደስታ ቢያውቁ ኖሮ ለኛ ነው የሚገባው ብለው ይጋደሉን ነበር" -ኢብኑ ተይሚያ